የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
ጥራቱን የጠበቀ ፍትሐዊና ተደራሽ የሆነ ጤና ማበልጸግ እና በሽታ መከላከል፤ የፈዉስ ህክምናና ተሃድሶ ጤና አገልግሎት ተልዕኮ እና ጤናማ፣ ምርታማና የበለጸገ ማኀበረሰብ የመፍጠር ራዕይን ዳር ለማድረስ ሰፊ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ ስለሆነምተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን መከላከል እና አክሞ ማዳን፤ የእናቶች እና ህጻናት ሞት መቀነስ፤ መሰረታዊ የጤና አገልግሎት ለሁሉም ዜጋ ማዳረስ ላይ መሰረት ያደረገ የጤና ፖሊሲ ተቀርጾ የህብረተሰቡን መሰረታዊ የጤና አገልግሎት ጥያቄ በተገቢ ሁኔታ ለመመለስ የተለያዩ ስትራቴጅክ እርምጃዎች ተቀርጸዉ እየተተገበሩ ይገኛሉ፡፡
የጤና ሴክተሩ አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት እና ተደራሽነትን በማሻሻል፤ በቴክኖሎጅ የተደገፈ ፈጣን እን ከብልሹ አሰራር የጸዳ የህክምና አገልግሎት በመስጠት ሁለተኛዉ የጤናዉ ሴክተር ትራንስፎርሜሽን አጀንዳን ለማሳካት ርብርብ እየተደረገ ይገኛል፡፡ .... ተጨማሪ ያንብቡ
አቶ አህመድ እንድረስ , የልደታ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ







