image
image
image
image
image

ህዳሴ ፍሬ ጤና ጣቢያ አምስተኛውን በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከበረ የሚገኘውን የመረጃ ሳምንት  "የጤና መረጃ እና በዲጅታል ጤና ፈጠራዎች ላይ ዘላቂ ኢንቨስትመንት በማድረግ የጤና ትሩፋቶችን ማሳደግ" በሚል መሪ ቃል ተከብሮ ውሏል።

ግንቦት, 2018 10, 2017
በልደታ ክፍለ ከተማ ውስጥ ካሉ ጤና ጣቢያዎች መካከል የሆነው ህዳሴ ፍሬ ጤና ጣቢያ አምስተኛውን በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከበረ የሚገኘውን የመረጃ ሳምንት  "የጤና መረጃ እና በዲጅታል ጤና ፈጠራዎች ላይ ዘላቂ ኢንቨስትመንት በማድረግ የጤና ትሩፋቶችን ማሳደግ" በሚል መሪ ቃል ተከብሮ ውሏል። በፕሮግራሙ ላይ ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ CBMP ፕሮጀክት፣ ከልደታ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት ባለሙያዎች እንዲሁም በልደታ ክፍለ ስር የሚገኙ የመረጃ አገልግሎት ባለሙያዎች እና ተወካዮች ተገኝተዋል። በፕሮግራሙም ላይ የህዳሴ ፍሬ ጤና ጣቢያ ሀላፊ የሆኑት ወ/ሮ የማታወርቅ ነጋሽ የ2018 የዘጠኝ ወር እቅድ አፈፃፀም ያቀረቡ ሲሆን በተጨማሪም የጥራት ማጠናከር ቡድን መሪ የሆኑት ወ/ሮ ሜሮን ዳታን፣ ቴክኖሎጂን እና EMR በተመለከተ ሰፊ መረጃዎችን አቅርበዉ ውይይቶችና የስራ ጉብኝቶችን በማድረግ ፍፃሜውን አግኝቷል።

መልዕክትዎን ይላኩ